Saturday, February 8, 2020

ክብደት ለመጨመር 12 ሳይንሳዊ መንገዶች

 ክብደት_ለመጨመር 12 #ሳይንሳዊ መንገዶች  

ክብደት መጨመር ክብደት ለመቀነስ ከሚደረገው ተግባር እኩል ተመሳሳይ ትጋት ይፈልጋል፡፡ ውፍረት ከሽብር አደጋ ባልተናነሰ የዓለማችን ስጋት በሆነበት ዘመን የተስተካከለ አቋም እንዲኖረን
በርካታ ጥረቶችን እናደርጋለን፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ከልክ በማለፍ ሁኔታ ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሰዎችም፣ ለበሽታ ሊኖራቸው
የሚችለውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ ለብሰው እንዲያምርባቸውና በሂደቱ ሊከሰትባቸው የሚችለውን ምቾት ማጣት ለማስወገድም እንዲሁ፣ ተጨማሪ ኪሎ በሰውነታቸው ላይ ለመጨመር
የመፍትሄ በሮችን ሁሉ ያንኳኳሉ፡፡

ባለሙያዎች ታዲያ፣ ከመፍትሄ አቅጣጫዎች የምናገኘው ስብ ወይስ ጡንቻ የሚለውን ቀድመን መለየት እንዳለብን ያስገነዝቡናል፡፡ አንዳንዶቹ በሰውነታቸው ላይ ስለሚጨምሩት ክብደት ትኩረት አይሰጡም፡፡ ጡንቻ፣ ስብ ወይም የሁለቱ ጥምረት፣ እነዚህ ሰዎች ከብዶና ወፍሮ መታየት ብቻ ስለሆነ ዓላማቸው ወደ ባሰ ሁኔታ ሊሸጋገሩ ይችላሉ፡፡ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች በተሻለ ሁኔታ ክብደት በሰውነታቸው ላይ መጨመር ስለሚችሉበት መንገድ፣ ከምርምር ውጤቶች የተገኙትን እነዚህ
መመሪያዎች በተቻለ መጠን ለመተግበር እንሞክር፡፡

1. በቀ3-5  ጊዜ መመገብ፡- 
ክብደት ለመጨመር በቀን ከ3 እስከ 5 ጊዜ መመገብ መጀመር ይኖርብናል፡፡ ታዲያ የመመገቢያ
ሰዓታችን በሚገባ መከፋፈል ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም በአንድ ጊዜ በምንወስደው ከፍተኛ ምግብ ሳቢያ ጨጓራችንም በስርዓት መፍጨት እንዳይችልና ሰውነታችን ሁሉንም ካሎሪዎች መቀበል
እንዳይችል ምክንያት ይሆናል፡፡

እርግጥ ነው በየ3 ሰዓታት ልዩነት የምግብ ፍላጎታችን ላይነሳሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን ጫን ብለን መመገባችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡ በየዕለቱም የምግብ ፍላጎታችን እያደገ ስለሚመጣ፣ መቸገራችን ይቀንሳል፡፡ በተቻለ መጠን ታዲያ በአመጋገባችን ውስጥ ጤናማ ምግቦችን መምረጣችንን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡

👉2. ክብደት የማንሳት ልምምዶችን  በሳምንት ሶስት ጊዜ ማድረግ ለወንዶች፡-
በክብደቶች በመታገዝ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ስንጀምር ጡንቻዎቻችንን ማሳደግ እንችላለን፡፡ በሂደትም የክብደቶቹን ሚዛን መጨመር ያስፈልጋል፡፡ ይሄ በተለይ ከሰውነት ክብደታችን ባሻገር ጥንካሬያችንን ማሳደግ እንድንችል የሚረዳን ነው፡፡በየሳምቱም ጥንካሬ ለመጨመር በጂም ውስጥ የምንሰራውን ኪሎ በየሳምቱ መጨመር ግዴታችን ነው። ከዛም ከጂም ውይም ስፖርት ቦታ ከወጣን ቡሃላ ጥሩ የተመጣጠነ መግብ በመመገብ ኪሎዋችን ሊጨር ይችላል ማለት ነው።
👉3. ከ300-500 ካሎሪዎችን ማከማቸት
ቀደም ሲል እንደተገለፀው፣ ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት፣ የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማግኘት የምንችለው፡፡ምክንያቱም እነዚህ ምግቦች ናቸው ትልቅ ካሎሪ በቀላሉ ሊሰጡን የሚችሉት። ስለዚህ በደንብ አድርገን እነዚህን ምግቦች በየቀኑ መመገብ ይኖርብናል። ሌላ በቀላሉ ካሎሪን ሊጨምርልን ይሚችል ደግሞ ጁስ እና አንደ በሶ አይነት ፈሳሽ ነክ ምግቦች ናቸው።


👉4.  ሁሉንም የሰውነት ክፍል ማሰራት፡-
በጂም ወይም በቤት ውስጥ ስፖርት የምንሰራ ወይም ክብደት የምናነሳ ከሆነ ሁሉም የሰውነት ክፍላችን በሚገባ እየሰራ መሆኑን ነው በቅድሚያ ማረጋገጥ ያለብን፡፡ ምክንያቱም ብዙዎቻችን ትኩረት የምናደርግባቸው ብዙ የጡንቻ ክፍሎች አሉንና፡፡ ስፖርቱን የሚጀምሩ ብዙ ሰዎች እጃቸውን ፣ ደረታቸው ወይም ትከሻቸውን አካባቢ ብቻ ትኩረት በመስጠት ልምምድ በማድረግ
ትልቅ ስህተት ይፈጽማሉ፡፡ ይሄ አካሄድ የሰውነታችን ሚዛን እንዲበላሽ በማድረግ ራሳችን በፍቅር የማንወደው ሰውነት እንድንላበስ ምክንያት ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው በስነ ስርዐት የታሰበበት ፕሮግራም የሚያስፈልግን። ለጀማሪዎች የሚመከረው ፕሮግራም በሳምንት ሶስት ጊዜ ልንሰራው የምንችለው የሙሉ ሰውነት ስራ ነው።



👉5.  በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር፡-
ቀደም ሲል እንደተገለፀው ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት፣ የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማሳካት የምንችለው፡፡ምክንያቱም ስፖርት በምንሰራበት ጊዜ ጡንቻችን በደቃቁ ጉዳት ይገጥመዋል። አይዞቹ ምክያቱም ይሄ ጥሩ ነገር ነው። ከዛም ግን ጉዳቱን ለመጠገን በፕሮቲን የበለፅገ ምግብ መመገብ ግድ አለብን።
👉6. ፕሮቲን ሼክ ፡- የተጠየቅነውን ፕሮቲን በመብላት ብቻ ሟሟላት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ፕሮቲን ሼክ በመግዛት በቀላሉ በቀን ውስጥ የሚያስፈልገንን ፕሮቲን ክምችት ማግኘት እንችላለን ማለት ነው። ነገር ግን ኢትዮፒያ ውስጥ ፕሮቲን ሼክ ወደድ ስለሚል ገንዘባችንን ጥሩ ጥሩ ምግብ በመግዛት ላይ ብናውጣው ይሻላል ብዬ እመክራቹሃለው።





👉8. ለማገገሚያ የተለያዩ  አማራጮችን መከተል፡-የማፍታቻ እንቅስቃሴዎች፣ሩጫ፤ ረጅም ወክ እና ፍጣን የአካል እንቅስቃሴዎች ሀፕታይት እንዲምጣ ስለሚረዱን በመጀመሪያ ከምግብ በፊት በመስራት ብዙ ምግብ እድንመገብ ያግዘናል ማለት ንው።

  8. በካርቦን ሃይድሬት የበለፀጉ ምግቦች፡- ካርቦሀይድሬት ማለት ሰውነታችን አንደ ሀይል የሚጠቀምበት የምግብ ተዋፅዖ ነው። ከካርቦሀይድሬት የተዎጣ ምግብ ከተመገብን ሰውነታችን በሀይል የተሟላ እና ለስፖርት ስራችን ትሩ ጥንካሬ በመስጠት ያግዘናል። ካርቦሀይድሬት እጥረት ግን ካለብን ሰውነታችን በቀላሉ የመድከም አና የሀይል እጥረት ያጋጥመዋል ስለዚህም ኪሎ ለመጨመር በደንብ ካርቦሀይድሬት እንመገብ። ካርቦሀይድሬት ያላቸው የምግብ ምሳሌዎች ዳቦ፤ሩዝ፤አንጀራ፤ሙዝ ዎናዎቹ ናቸው።



👉9.  በራሳችን ላይ ትዕግስት ይኑረን፡-
ጤናማ ባልሆነ አካሄድ በፍጥነት ተጨማሪ ክብደትን ማግኘት ተጨባጭ አይደለም፡፡ነገር ግን ኪሎ ብቻ ለመጨምር ብለን ፕሮሰስድ የሆኑ መግቦችን ብቻ መመገብ ጥፋት ነው። የተመጣጠነ ንፁህ ምግቦች ተመግበን ነው ኪሎ መጨመር ያለብን። ካልሆነ ግን የበሽታ ውፍረት ነው የሚሆንብን።
የተቀመጡ መመሪያዎችን በመከተል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ2-4 ኪሎ ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው፡፡ ባለሙያዎች ፈጣን ለውጥ ካላገኘን በቀላሉ ስሜታችን ሊጎዳብን አይገባም ይሉናል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሰው ሰውነት ልዩነት ስላለው፡፡


👉10.  በራስ መተማመን፡- ክብደት ለመጨመር ያወጣነው ዕቅድ ክብደት የሚለካው ለስኬታማነቱ በራሳችን ላይ ያለን መተማመን ነው፡፡ ከጠንካራ ሥራ በኋላ ለውጥ ማየት ባንችልም፣ ሌላና እጅግ ጠንካራ ወደ ሆነ ልምምድ መግባት ይኖርብናል፡፡ተጨማሪ ምግብ መመገብ፣ ተጨማሪ ክብደቶችን ማንሳት፣የውስጥ ጥንካሬን አስጠብቆ መቆት ናቸው፣ ክብደት መጨመር ከሚፈልግና በራሱ ከሚተማመን ሰው የሚጠበቀው፡፡

11. #ረዥም ርቀት መሮጥ ውጤት የለውም፡-
መሮጥ ግዴታ ከሆነ አጫጭር ርቀቶችን እና አቀበቶችን መውጣት ነው ተመራጩ፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የአጭር እና ረዥም ርቀት ሯጮችን ሰውነት መመልከት ነው፡፡ የትኛውን ነው መሆን የምፈልገው? በማለት ራስን መጠየቅ ደግሞ መሰረታዊ ነው፡፡


👉12. #መተኛት፡-
ከፍተኛ ክብደት ለመጨመር በቀን ቢያንስ 8 እና 9 ሰዓት መተኛት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ ሰውነታችን ምንም ስራ እንዳይሰራ በማድረግ በተኛበት ጡንቻ እንዲገነባ እናስችለዋለን፡፡ በቀን ውስጥ ከ6 እና ከዚያ በታች እንቅልፍእያገኘን ከሆነ፣ በአመጋገባችንና በስፖርት እንቅስቃሴዎችያመጣናቸውን ለውጦች ማስጠበቅ አንችልም፡፡ ስለዚህም ጥሩ የሆነ እንቅልፍ በማግኘት ኪሎ አና ጡንቻን እንገንባ።






ስሜ አቤል ይባላል የአካል ብቃት ባለሞያ ነኝ ይሄ ቀጠቀማቹ ወይንም ትያቄ ካላቹ ኮሜንት አድርጉልኝና እመልስላቹሃለው። ለወደፊት ሌላ ፅሁፍ ይዜ እመጣለሁ።

ይሄን ቻናል በመቀላቀል ይበልጥ        ይማሩ EthiopianUltraphysique 

No comments:

Post a Comment